Our Monastery

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

“ከዱሮ ዘመን የፈረሱት ስፍራዎች ይሠራሉ፥ የብዙ ትውልድም መሠረት ይታነጻል፤ አንተም፦ ሰባራውን ጠጋኝ፥ የመኖሪያ መንገድን አዳሽ ትባላለህ።” (ኢሳ 58፥12)
ሐመረ ብርሃን ቅዱስ አባ ሳሙኤል ገዳም እንዴትና ለምን ተመሠረተ?
የሐመረ ብርሃን ቅዱስ አባ ሳሙኤል ገዳም አጀማመሩ በሰሜን አሜሪካን ተወልደው ወይም በልጅነታቸው መጥተው ያደጉ ወጣቶች “አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር” (2ኛ ጢሞ 3፥14) እንደተባለ እግዚአብሔርን አውቀው በእግዚአብሔር ፍቅር መኖር እንዲችሉ በተከፈተላቸው የሐሙስ የሰርክ ጉባኤ መነሻነት ነው።
እንዲሁም እነዚህን ብቻ ሳይሆን ትምህርት ቤቱን አሳድጎ መጪውን ትውልድ በትምህርት እየኮተኮቱ በእግዚአብሔር ቤት ለማሳደግ ከተማሩም በኋላ ከራሳቸው አልፈው ተርፈው ወደ አገግሎቱ የሚገቡ ወጣቶች የሚቀርቡበትን መንገድ ማበጀት አስፈላጊም ስለሆነ ይህንና የመሳሰሉትን ሃሳቦች ታሳቢ በማድረግ ለትምህርትና መንፈሳዊውን ሕይወት መለማመጃ የሚሆን ገዳም የግድ አስፈልጓል።
ዛሬ ላይ ሆነን ለመጪው ትውልድ ታአሪክና ሃይማኖቱን እንዲወርስና እንዲያስቀጥል አስተካክለን አዘጋጅተን ካላስረከብነው ማንነቱ ሊጠፋበት ስለሚችል ይህን የሚሠራ ገዳምና ማሰልጠኛ አስፈልጓል።
መቼ ተመሠረተ?
ይህ ገዳም በልዩ ልዩ ምክንያቶች በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ቆየት ያለ ቢሆንም እንቅስቃሴው ወደመተግበር የተጀመረው ግን ወደ ስምንት ዓመት ይሆነዋል። የተለያዩ እናቶችና አባቶች ወደሌሎች እንደካቶሊክ የግብፃውያን የሆኑ ገዳማት እየሄዱ የሁለት የሦስት ቀን እረፍት አድርገው ሲመለሱና ሲነግሩን የራስ ቦታ ቢገኝ ደግሞ የሚያሰኝ እቅድ እንዲፈጠር ከእለ ከተጠቀሰው ሃሳብ ጋር ከመነጫው መካከል አንዱ ምክንያትምና ለሃሳቡ መነሻም ሆኖአል። በተጨማሪም መነኮሳት አባቶች በአግልግሎትም ይሁን በሆነው ምክንያት ሃገርቤት ካልሄዱ በስተቀር በከፋቸው ግዜ እንኳን የእረፍት ግዜና ቦታ ባለመኖሩ ብዞዎቹ ተጎድተዋል።ለአሳ ሕይወቱ በባሕር መገኘት እንደሆነ ሁሉ ለመንኩሴም ሕይወቱ ገዳም ነውና።
ከላይ እንደተገለጸው ወጣቶችም ቢሆኑ ለመንፈሳዊ አገግሎት እራሳቸውን ቢሰጡ ወደሃገር ቤት ለመንፈሳዊው ትምህርት ሲሄዱ ስለሚከብዳቸው ወደኋላ እንዳይሉ ገዳሙ የምናኔ ቦታ ብቻ ሳይሆን ትምህርት ቤትም ጭምር እንዲሆን ታቅዶ ነው መመሥረት ያስፈለገው። ከላይ በተጠቀሰው ዓመት ታስቦ እቅስቃሴው በዚህ ሃገር ያሉትን የገዳማት እንቅስቃሴን መቃኘት ተጀምሮ ፈቃድ የማግኘት ሂደቱ ቀጥሎ በዲሤምበር 2015 የመጀመሪያው ፈቃድ ከአሜሪካን መንግሥት ተገኝቷል።

የገዳሙ እውቅናና ሕጋዊነት
ይህ ገዳም የሀገሪቱ ለሃይማኖት የተሰተው ሕግ በሚያዝዘው መሠረት ከኮመንዌልዝ ኦፍ ቨርጂኒያ ሙሉ ፈቃዱን ከአገኘን በኋላ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል አቅርበን ቡራኬ ሙሉ ፈቃድ ተቀብለናል። 
ከዚህ በመቀጠል ቦታው ከተገዛ በኋላ ምን ዓይነት ይዘት ይኖረዋል? በቦታው ላይ የሚሰጡ አገልግሎቶች ምን ምን እንደሆኑ፣ሊሟሉ የሚያስፈልጉ ቦታውን ለአገግሎት ብቁ ሊሆን እስከምሚችል ድረስ ከደጋፊ አካላት የሚጠብቁትን የቦታው ይዘት፦
ገዳማችን የሚመሠረተው ዓላምውም ይሁን ይዘቱ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን የክህናት ማሰልጠኛ የዛሬው ኮሌጅን አብነት ያደረገ ነው። የተለያዩ የገዳማት ቅርጾች/ሥርዓቶች/ አሉ። ከቅርጾቹ/ከሥርዓቱ/ አንዱ የአንድነት ገዳም የሚባለው ነው። የዝዋይ ገዳማችንም ይህ ቅርጽ ያለው በመሆኑ እኛ ይህንን ቅርጽ ነው የምንከተለው።ስለዚህ ገዳማችን የአንድነት ገዳም ሆኖ ይቋቋማል ማለት ነው።

ቦታው ሲግውዛ የቅድሚያ ዝግጅት
ቦታው ከተገዛ በኋላ ቅድሚያ የሚሰጠው ትልቁ አባት አባ ጎርጎርዮስ የዝዋይ ሐመረ ብርሐን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን ሲመሠርቱ ቤተክርስቲያን ከመሥራታቸው በፊት የእንግዶች ማረፊያ ነው የሠሩት። ቤተክርስቲያን የሚሠሩም ይሁን ገዳሙን የሚረዱ እንግዶች መጀመሪያ ማረፊያ ያስፈልጋቸዋል በማለት።የሚገርመው ደግሞ እኛ እግዚአብሔር ቢፈቅድልን በእንግድነት የሚመጡም ይሁኑ በአገግሎት የሚሳተፉ የተገኘው ቦታ ይዘት ሁሉም ነገር የተዘጋጀ ነው።ቦታው እንደተገዛ የመጀመሪያ ሥራችን ለእንግዶችና ለአገጋዮች ማረፊያን ማመቻቸት ይሆናል ማለት ነው።

ገዳሙ ውስጥ ለተገልጋዮች በየደረጃቸው የሚሰጡ አገግሎቶች ሥርዓታቸው፦

show more

1. የገዳሙ ዕቅድ የንግዶች ቤት ሲዘጋጅ ከሁሉ በፊት ሥርዓተ ገዳም በሚፈቅደው መሠረት የወንዶችንና የሴቶችን ማረፊያ በመለየት ለሱባኤ/ለጸሎትም/ ይሁን ለአገግሎት ለሚመጡ ምእመናን የሚሆን ሥፍራ ማዘጋጀት የመጀመሪያው ሥራችን ይሆናል።
2. አቅም በሚፈቅደው መሠረት የአብነት ትምህርቶች የሚሰጡበትን መሠረታዊ ነገር በማሟላት ሁኔታዎች ያመቻቻል።
3. ከዚህም ሌላ የተለያዩ የበገናና የመሳሰሉትን ሃገሩን ሊመጥን ቤተክርስቲያናችንና ሃገራችንም ሊያስተዋውቅ የሚችልበትን መንገድ በማሰናዳት ትምህርቱ እንዲሰጥ ለማድረግ ሃሳቡ አለን።
4. እንደዚሁም ገዳሙና የአካባቢውን አብያተ ክርስቲያናትን ሊረዱ የሚችሉ ልዩ ልዩ የምሥጢራት መፈጸሚያና አዘጋጅቶ ለማቅረብና በተጨማሪም የእደ ጥበባት ውጤቶችን የሆኑትን እንደ ዕጣንና ሌሎችም ንዋያተ ቅድሣት የራቀውን በማቅረብ፣ መዘጋጀት የሚቻለውን ደግሞ በማዘጋጀት ለማቅረብ ገዳሙ ይተጋል።።
5. በሰሜን አሜሪካና በሌሎችም ክፍለ አለማት ያሉትን ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ፍጹም በሆነ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት የታነጹ ሆነው ለዓለማችን መልካም ሆነው መልካም እንዲሠሩ ከራሳቸው አስተማሪዎችን መልምሎ ተገቢውን ኮርስ አዘጋጅቶ ማሰልጠንና አሰልጣኞችንም በማውጣት ግብረ ገብነት ያላቸው ወጣቶችን መፍጠር ሌላው ዓላማችን ነው።ለአዲሱ ትውልድ የግድ ከራሱ የወጣ አስተማሪ ስለሚያስፈልገው።
6. ከሁሉም በላይ በየቤቱ፣በእስር ቤት፣በልዩ ልዩ ሱስና ጥገኛ በሆነ ክፉ አመለካከት ተይዘው ያሉ ወጣቶችን ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን በሚያስፈልገው ሁሉ የባህርይ ለውጥ አምጥተው እንደዚሁ ከህብረተሰቡ ጋር በመልካም ግንኙነት አንድ ሆነው እንዲገለገሉ ማገገልም እንዲችሉ ማድረግም የገዳሙ ተጨማሪ ዓላማና ዕቅድም ነው።
7. በተጨማሪም የወጣቶች ጉዳይ ብቻ ሳይሆን አረጋውያን አባቶችና እናቶች መንፈሳዊ እንክብካቤ በማጣት በብዙ ችግር እንደሚኖሩ የታወቀ ነውና የነርሱም ጉዳይ የሚታሰብበትና የገዳሙ ምናልባትም የረጅሙ ግዜ ዕቅድ ሊሆን ይችላል።
8. ለምእመናን ሁሉ እንደ አስፈላጊነቱ የምክር አገግሎትና ለንስሐ፣ለጋብቻ ለመሳሰሉት ተገቢውን ትምህርት ሰጥቶ ለሚዘጋጁበት የሕይወት ጉዞ ሁሉ በኮርስ መልክ ትምህርት መስጠትና ለክብር ማብቃት ገዳሙ አቅዷል።
9. ሊገዛ በድርድር ላይ ያለው ቦታ 187 ኤከር መሬት ሲሆን አሁን ባለበት ሁኔታ በአንድ ጊዜ ከ20 ያላነሱ መኝታ አልጋ የሚይዙ ክፍሎች፣ 8 የተሟሉ መታጠቢያ ክፍሎች፣ የተሟላ ትልቅ ኪችን፣ ትልቅ የሰብሰባ አዳራሻና መማሪያ ክፍሎች፣ አንድ ቤተ ክርስቲያን፣ በቢሮ መልክ የሚያገለግሉ ክፍሎች፣ የእርሻና የከብት ማርቢያ ስፍራዎች፣ ሐይቅ፣ ከብዙ በጥቂቱ ሲሆን ቦታው እንደተገዛ በአጭር ጊዜ ውስጥ ገዳሙ በይፋ ስራውን ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።
ቦታው ለአገግሎት ብቁ እስሚሆን ድረስ ከደጋፊዎች የሚያስፈልጉ ነገርሮች ፦
• ገዳሙ ራሱን ችሎ በራሱ መንቀሳቀስ እስከሚችል ድረስ የዚህ በረከት ተካፋይ መሆን የሚፈልጉ ሁሉ ባለው ማገልገል ይችላል።እውቀት ያለው በእውቀቱ፣ጉልበት ያለው በጉልበቱ፣ገንዘብ ያለው በገንዘቡ ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ የዚህ ታሪካዊን የገዳም ምሥረታ ሥራ ላይ በመሳተፍ አሻራውን በማስቀመጥ በአምላኩ ዘንድ በመዝገበ ሕይወቱ ስሙን ያጽፍ።
• ይህን ሥራ ሥራውን ለማስጀመር እንዲቻል በቅድሚያ ቦታውን የራስ ማድረግ ያስፈልጋል።ቦታውን ለመግዛት $750,000 ስለተጠየቅን በድጋፍም ሆነ በብድር ህን ማግኘት ግድ ነው።ይህን ገንዘብ ማግኘት በምንችለውና እግዚአብሔር በመራን አስተባብረን እንድንከፍል ይህን መልእክት የምታነቡ ሁላችሁም መልእክቱን ላልደረሰው እያደረሳችሁ የበረከቱ ተካፋዮች እንዲሆኑ ታደርጉ ዘንድ በጻድቁ በአባ ሳሙኤል ሥም እንጠይቃችኋለን።
• በመዝሙር 126፥127 ”እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፥ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፥ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል። “ እንደተባለ ሁላችንም ለሥራው ምክንያቶች እንጂ ዋናዎች አይደለንም። እርሱ ሁሉን የሚችል አምላክ በሃገራችን ኢትዮጵያ ብዙ ምክንያት አድርጎ ብዙ ታላላቅ የታሪክ ቦታዎችና ታላላቅ ሥራዎች ያሰራቸው ብዙ ሰዎች ነበሩት። ዛሬ ሁሉችንም መመኘትም ሆነ መጸለይ ያለብን ነገር ቢኖር የነዚያ ደጋግ አባቶችና እናቶች አምላክ እኛንም ምክንያት አድርገኸን ይህን ሥራ ጀምረን እንድንፈስም እርዳን ብለን ጸሎታችንን እናድርግ። አምላከ ቅዱስ ሳሙኤል ሥራችንን ይባርክልን

“ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት። (ገላ 6፥9)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

show less