ገብር ኄር (የዐቢይ ጾም ስድስተኛው ሳምንት)

Great Lent Sixth Sunday Gebre Here ገብር ኄር (የዐቢይ ጾም ስድስተኛው ሳምንት)

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስያሜ የዐቢይ ጾም ስድስተኛው እሑድ ወይም ሳምንት ገብር ኄር ይባላል፤ ስያሜውን የሰጠውም ኢትዮጵያዊ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡  ከአምስቱ መጻሕፍቶቹ አንዱ በሆነው ጾመ ድጓ የዐቢይ ጾም ሳምንታት ስያሜዎች ከነሥርዓተ ማኅሌቱ አዘጋጅቷል፡፡ ስለዚህ በስድስተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ከዋዜማው ቅዳሜ ጀምሮ በቤተ ክርስቲያን የሚዘመረው ዝማሬ፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚሰጠው ትምህርት ገብር ኄርን  ወይም ታማኝ አገልጋይን የሚያወሳ ነው፡፡

ለዚህም ምሳሌ እንዲሆነን በማቴዎስ ወንጌል ላይ የተጻፈው ታሪክ እናነሳለን፤ አንድ ባለ ጸጋ ሰው ባሪያዎችን ጠርቶ ለአንዱ አምስት መክሊት ሰጠው፣ ሁለት መክሊት የሰጠውም አለ፣ አንድ መክሊትም የሰጠውም አለ፡፡ ከዚህ በኋላ ወደሩቅ አገር ሄደ፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለውም ወጥቶ ወርዶ ሌላ አምስት አትርፎ ዐስር አደረገ፡፡ ሁለት የተቀበለውም አትርፎ አራት አደረገ፡፡ አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ መሬቱን ቆፍሮ በሻሽ ጠቅልሎ የጌታውን መክሊት ቀበራት፡፡

ከብዙ ጊዜ በኋላ ጌታቸው መጥቶ ተቆጣጠራቸው፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለው ቀርቦ ‹‹ጌታዬ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ አምስት አተረፍኩ አለው፡፡ ‹‹ገብር ኄር ወምእመን ዘበሁድ ምእምነ ኮንከ ዲበ ብዙህ እሰይመከ ባዕ ውስተ ፍስሐሁ ለእግዚእከ፤ አንተ ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃል፤ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ›› አለው፡፡ ሁለት የተቀበለውም ቀርቦ ‹‹ጌታዬ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ ወጥቼ ወርጄ ሌላ ሁለት አትርፌ አራት አድርጌአለሁ፡፡ አንተ ታማኝ በጎ አገልጋይ በጥቂቱ ታምነሃል፤ በብዙ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ›› አለው፡፡ አንድ መክሊት የተቀበለው ግን ቀርቦ ‹‹ጌታዬ አንተ ክፉና ጨካኝ ካልዘራህበት የምታጭድ ካልበተንህበት የምትሰበስብ እንደሆንክ ስለአወቅሁ መሬቱን ቆፍሬ ቀበርኋት እነኋት መክሊትህ አለው፡፡ አንተ ሰነፍ ባሪያ መክሊቴን በጊዜ ልትሰጠኝ በተገባህ ነበር፤ እኔም ወጥቶ ወርዶ ለሚያተርፍ በሰጠሁት ነበር፡፡ የዚህን መክሊት ውሰዱና አስር መክሊት ላለው ስጡት፡፡ላለው ይሰጡታል ይጨመርለታል፤ለሌለው ግን ያለውን ይቀሙታል፡፡ይህን ሰነፍ ባሪያ እጅ እግሩን አሥራችሁ ጽኑዕ ጨለማ ወደአለበት ውሰዱት፤ጩኸትና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበትም ጨምሩት››አለ፡፡(ማቴ.፳፭፥፲፬-፳፭)

ባለ ጸጋ የተባለው ጌታ ነው፤ መክሊት የተባለው ልዩ ልዩ የአገልግሎት ጸጋ ነው፡፡ ያተረፉት በሚገባ በታማኝነት ያገለገሉ ቅዱሳን ሰዎች ናቸው፤ መክሊቱን የቀበረው ደግሞ በታማኝነት በተሰጠው ጸጋ ማገልገል ሲገባው ያላገለገለ ነው፡፡ ጌታቸው ሊቆጣጠራቸው መጣ ማለት በዕለተ ምጽአት ለሁሉም በአገለገለው አገልግሎት ዋጋ ለመስጠት እንደሚመጣ ያሳየናል፡፡ያገለገሉትን ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አላቸው ማለት ታማኝ አገልጋዮች መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉና፡፡ ሰነፎች ደግሞ ጥርስ ማፋጨት ስቃይ ጽኑዕ ጨለማ ባለበት ሲዖል መግባታቸውን የሚያሳይ ነው፡፡

ከላይ ያነሳነው የቅዱስ ወንጌል ቃል ‹‹ታማኝ አገልጋይ ማነው?›› ይህ እያንዳንዱ በአርዓያ እግዚአብሔር የተፈጠረ የሰው ልጅ ጥያቄ ነው፤ የዚህን አምላካዊ ጥያቄ መልስ መስጠት ከሰው ልጆች ይጠበቃል፡፡

ምንባባት

መልዕክታት 

2ኛ ጢሞቲዎስ ምዕራፍ 2÷1-16

1ኛ የጴጥሮስ መልእክት ምዕራፍ 5: 1-12

ግብረ ሐዋርያት :- ሐዋ. 1÷6-9

ምስባክ:- መዝ.39÷8  

ከመ እንግር ፈቃድከ መከርኩ አምላኪየ፤ ወሕግከኒ በማእከለ ከርስየ። ዜኖኩ ጽደከ ባማኀበረ ዐብይ፤

ትርጉም፦ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ፥ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው። በታላቅ ጉባኤ ጽድቅን አወራሁ፤ 

ወንጌል :- ማቴ. 25÷14-31 

ቅዳሴ: – ዘባስልዮስ

The Sixth Sunday Gebre Here: Faithful Servant

Reading: Saint Matthew 25: 14 – 25

In the sixth great theme in the fast we asked, “Who is the wise and faithful servant?” The answer to this question is what we do or don not do with our lives until we await Christ’s return to this world in His second coming. The faithful servant is the person who hears and does or fulfills the word of GOD; it is the one who is faithful and loyal to God, the Church and its family; it is the person who has received the tradition and faith of Christ’s Church and holds it steadfastly and courageously. It is the person who is faithful over small things such as fasting, prayer, humility, devotion, our health and material wealth for use in GOD’s work on Earth. The faithful and good servant is the one who builds his house on the rock and not the sand. The unfaithful servant is the opposite of all these.

In the Great Fast, our Forefathers chose these third of four parables recorded by St. Matthew to explain Jesus’ teaching about the meaning of life. He taught that the basis of life’s tests is one’s use of talents. God gives us talents to develop according to His will. He observes what we do with these gifts, in the time of our lives. How one invests his or her potential in time indicates one’s attitude toward God, including one’s reactions unto others, to whom He has given different gifts. (Mt. 22:37- 41) While people often make the mistake of counting and comparing how many things they acquire by use of these talents, God is watching, on a more basic level, how the talents are invested, as either multiplying talents_ not stuff_ or as burying the talents in the stuff.

 Readings:

2 Timothy 2: 1 – 16

1Peter 5: 1 – 12

Acts 1: 6 – 9

Psalm 49.2  

To do Thy will, O my God, I am determined to do it. Indeed, Thy law permeates my system. (Geez = [it is] in the middle of my belly) I have preached righteousness in the great gathering.”

Matthew 25: 14 – 31

Liturgy: Anaphora of St. Basil